የሉፄ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2017 የትምህርት ዘመን ማጠቃለያና የወላጆች በዓል፣ ዛሬ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ! 🎉🎈

በመሐግብሩ ላይ የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል የመንግስት ተጠሪ አቶ ቦረና ቦላዶ የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደግፌ ኃይለማርያም ፣ የጎፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መጎስ መኩሪያ፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ የተማሪ ወላጆች፣ መምህራን፣ተማርዎችና የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብና የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር ሠራተኞች ተሳታፊዎች ነበሩ። በመረሐ -ግብሩ የተሳተፉት የጎፋ ዞን ምክትል የመንግስት…

ጎዕብማ የልማት ሥራ ትብብር ተፈራረመ

ጎዕልማ ፎሪአፍርካ(ForAfrika) ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር አብሮ ለመሥራት የልማት ትብብር ውል ተፈራረመ። ይህ ግብረሰናይ ድርጅት በአካባቢ ጥበቃ፣ በውኃ፣ በምግብ ራስን መቻል፣ የአደጋ ስጋት ሥራዎች ላይ የምሠራ ሲሆን አሁን ከማህበራችን ጋር በአካባቢ ጥበቃ እና በምግብ ራስን መቻል ላይ ትኩረት አድርጎ ለመሥራት የውል ሰነድ ተፈራርሟል። ማህበራችን አቅም በፈቀደው በትምህርት ፣በጤና፣ በሰብዓዊ ፣ በባህል እና በማህበራዊ ዘርፎች በርካታ…

በክልሉ የሚገኙ የልማት ማህበራት ህብረተቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመስራት መትጋት እንደሚገባቸው ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለፁ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር የተዘጋጀ የማህበረሰብ መድሃኒት መደበርን መርቀው ስራ አስጀመሩ። ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የማህበረሰብ መድሃኒት መደብሩን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት አገልግሎት መስጠት የጀመረው የመድሃኒት መደብር ህዝብ ከተባበረ የማያሳካው የልማት ተግባር አለመኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል። ለሁሉም ነገር መነሻው ሀሳብ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በየአካባቢው የሚከፈቱ የማህበረሰብ…

የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር ሥራአስኪያጅ አቶ ደግፌ ኃ/ማርያም አዲሱን ዓመት አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።

አቶ ደግፌ ኃ/ማርያም ለመላው የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሠላምና በጤና አደረሳችሁ ። አዲሱ ዓመት የሠላም ፣ የፍቅርና የስኬት እንድሆንልን ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ። በድጋሚ ለመላው አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ። የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት መስከረም 1/2017 ዓ.ም

በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቋም የድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቋም የድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄዷል፡፡ በአደጋው ሕይወታቸው ላጡ ዜጎች የ40 ቀን መታሰቢያና ከአደጋው የተረፉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያግዝ የገቢ ማሰባሰቢያ እንዲሁም አደጋውን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ላደረጉት ድጋፍ የምስጋና መድረክ ነው በመዲናዋ የተካሄደው፡፡ የድጋፍ ማሰባሰቢያና የምስጋና…

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር የ 15 ሚልየን ብር ድጋፍ አደረገ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር በአባቢው ላይ እያከናወነ ያለውን ልማታዊ ተግባራትን በዘላቂነት ለማገዝ ያስችል ዘንድ የልማት ማህበሩ #የቦርድ_አባላት (ሥራ አስፈፃሚ ዎች) ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል። የሚዲሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተወካይ አቶ ያዕቆብ ፍቄ ተቋማቸው የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር በዞኑ በመንግሥት የማይሸፈኑ የልማት ሥራዎችን እየሠራ ያለ ማህበር በመሆኑ ልማት ማህበሩን ለማጠናከር…

አቶ አሸብር_ብርሀኑ ለሉጼ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማጣቀሻ መጽሐፍት ድጋፍ አደረገ።

አቶ #አሸብር_ብሪሀኑ በ2016 ትምህርት ዘመን በወላጆች በዓል ላይ ተገኝተው ቃል የገቡትን ለሉጼ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ ማጣቀሻ መጽሐፍት ድጋፍ አድርገዋል። የሉጼ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ተግባር ውጤታማ እንዲሆን የዞኑ ተወላጆችና የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር ደጋፊዎች የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ዋና ሥራአስኪያጁ ጥሪውን ያቀርባል።