የሉፄ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2017 የትምህርት ዘመን ማጠቃለያና የወላጆች በዓል፣ ዛሬ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ! 🎉🎈
በመሐግብሩ ላይ የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል የመንግስት ተጠሪ አቶ ቦረና ቦላዶ የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደግፌ ኃይለማርያም ፣ የጎፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መጎስ መኩሪያ፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ የተማሪ ወላጆች፣ መምህራን፣ተማርዎችና የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብና የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር ሠራተኞች ተሳታፊዎች ነበሩ።
በመረሐ -ግብሩ የተሳተፉት የጎፋ ዞን ምክትል የመንግስት ተጠሪ አቶ ቦረና ቦላዶ በልማት ማህበሩ አማካይነት በት/ቤቱ እነተከናወነ ያለውን የልማትና እንዲሁም የትምህርት ልማት ተግባራትን በማድነቅ ቀጣይ በአገር አቀፍ ፈተና የሉጼ ተማሪዎች የላቄ ውጤት እንድያስመዘግቡ ተስፋ እንደምጣልባቸውና ይህ እንድሆንም ሁሉም አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንድያደርግ አሳስበዋል።
የጎፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላ አቶ ሞገስ መኩሪያም በትምህርት ዘርፉ መምሪያ እየሠራ እንደቆየና ይህም የምቀጥል እንደሆ አሳስበዋል።
የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ደግፌ ኃይለማርያምም የሉፄ ት/ቤት የሕዝቡ እንደሆነና የሕዝቡን መልካም ስም የሚያስጠራ ሆኖ እንድቀጥል ከተፈለገ የሁሉም አካላት ድጋፍ ተጠናከሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል ።
በመረሐ -ግብሩ በትምህርት የላቄ ውጤት ለመጡና በሥራ አፈፃፀሚ የላቄ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ሠራተኞች የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
በመርሐግብሩ ላይ :-
👉በተማሪዎች የቀረቡ የቴክኖሎጂ እና የጥበብ ስራዎችና ትርኢቶች 🎭
👉የወላጆችና የአስተማሪዎች አብሮነትና ውይይት 🤝
እንድሁም የልማት ማህበሩ የበጎ ቡድን አባላት ለተማሪዎች አስተማሪና ለቀጣይ ተግባራቸው ከሁሉ ጊዜ በላይ እንድነሳሱ የሚያደረጉ ከአድስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ ተማርና የአድስ አበባ ተማሪዎች ህብረት ምክትል ፕረዝዳንት ተማሪ ቴድሮስ ነጋሽ እና ከአ/ምንጭ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት ተማሪ የሆነው ተማሪ በሃይሉ ቤልጅጌ ለተማሪዎች አነቃቂ፣ አስተማሪ እና አስፈላጊ ምክር ለግሰዋል ።
መረሐ -ግብሩ ተማሪዎች የትምህርት ጊዜያቸውን በትጋትና በታታሪነት አጠናቀው ፣ የድካማቸውን ፍሬ የሚያጭዱበት ፣ ለወላጆቻቸውም ኩራት የምትሆኑበት ልዩ ቀን ነው ።
ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለመላው የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ፣ ለዚህ ስኬት ላበረከታችሁት አስተዋፅኦ ሁሉ ልባዊ ምስጋና እናቀርባለን! 🙏
ሉፄ ሁላችንም በትብብር ስንሰራ ምን ያህል መሄድ እንደምንችል ማሳያ እንደሆነና የ2018 የትምህርት ዘመን ይበልጥ ስኬታማ እንዲሆን አብረን እንስራ እንላለን ።








