በክልሉ የሚገኙ የልማት ማህበራት ህብረተቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመስራት መትጋት እንደሚገባቸው ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለፁ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር የተዘጋጀ የማህበረሰብ መድሃኒት መደበርን መርቀው ስራ አስጀመሩ።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የማህበረሰብ መድሃኒት መደብሩን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት አገልግሎት መስጠት የጀመረው የመድሃኒት መደብር ህዝብ ከተባበረ የማያሳካው የልማት ተግባር አለመኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል።

ለሁሉም ነገር መነሻው ሀሳብ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በየአካባቢው የሚከፈቱ የማህበረሰብ መድሃኒት መደብሮችን ህብረተሰቡ “የኛ መድሃኒት ቤት ” ብሎ ሊቀበል ይገባል ብለዋል።

የልማት ማህበራት ሲጠናከሩ የህዝቡን የልማት ክፍተቶች ይሸፍናሉ ያሉት አቶ ጥላሁን ከበደ የልማት ማህበራት ከአከባቢው አስተዳደርና እና ከክልሉ መንግስት ጋር በመቀናጀት የተሻሉ ተግባራት ለማከናወን መትጋት እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።

እንደ ክልል በርካታ ሀብትና ፀጋ ቢኖርም መጠቀም እንዳልተቻለ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን አንድነታችንን በማጠናከርና ህዝቡን በማስተባበር ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን መጀመር እንደሚገባም አሳስበዋል።

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የማህበረሰብ መድሃኒት መደብር መከፈቱን ተናግረዋል።

የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር የማህበረሰብ መድሃኒት ቤቶች እንዲከፈቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል ያሉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ መደብሮቹ ለህብረተሰቡ የተለያዩ መድሃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ ይገኛል ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማዬሁ ባውዲን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር ፕላቲንዬም አባል ሆነዋል።

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *