ራዕይ
የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር ራዕይ የጎፋ ህዝብ የልማት አንድነት ተጠናክሮ በህዝቡ ሰፊ ተሳትፎ ኑሮዉ በዘላቂነት ተለዉጦ፣ ከድህነት ነፃ የልማት፣ የሰላም ተምሳሌት፣ ጤናማ አካባቢና የበለጸገች ጎፋን ማየት ነዉ፡፡
ተልዕኮ
በሀገሪቱ የዕደገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እና በማህበሩ የልማት ስትራቴጂ መሠረት በከፍተኛ ቁርጠኝነት ሁሉንም የልማት አቅሞች (መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ደጋፊዎች፣ ወዳጆች፣ ከህብረተሰቡና በአካባቢዉ የሚገኘዉን እምቅ ሀብት ወዘተ…) በማቀናጀት ሕብረተሰቡን ለልማት በማነሳሳትና በማሳተፍ ለጎፋ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለዉጥ ለማምጣት ችግር ፈቺና በህብረተሰቡ የልማት ፍላጎት ላይ አትኩሮ አጠቃላይ ዕድገትን የሚያፋጥኑ ተግባራት አከናዉኖ ለዘላቂ ልማት ተግቶ ይንቃሳቀሳል፡፡
እሴቶች
ተጠያቂነት፣ አሳታፊነት፣ ግልጸኝነት፣ ተወዳዳሪነት፣ ቁርጠኝነት፣ ሀቀኝነት፣ ሥነ ጾታዊ እኩልነት፣ ፍትሀዊነት እና የቡድን ስሜት የማህበሩ መሠረታዊ እሴቶች ናቸዉ፡፡
ዓላማ
የህዝብ ተሳትፎን በማረጋገጥ በየደረጃዉ ያለዉን የህብረተሰብ ክፍል የልማት ማህበሩ የሀብት ምንጭ እንዲሆን በማድረግ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ ትብብር በመፍጠር የህዝብ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን ነዉ፡፡