
Coming…
Coming…
- በዞኑ የመጀመሪያ የሆነዉን በልማት ማህበሩ የሚመራ የጎበዝ ተማሪዎችን ማዕከል ሉጼ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2015 ዓ/ም በመክፈት በአሁኑ ወቅት በ9ኛ እና 10ኛ ክፍሎች ወንድ 83 ሴት 29 ድምር 112 ተማሪዎችን በመያዝ የትምህርት ሥራዉ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
- የትምህርት ሥራዉን የተሳካ ለማድረግ ለትምህርቱ ሥራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሟላት በተደረገዉ ጥረት የማጣቀሻ መጽሐፍት፣ ኮምፒዩተሮች፣ የተማሪ እና የመምህራን መቀመጫዎች፣ የመጽሐፍት ማስቀመጫ ሸልፎች፣ ፎቶ ኮፒ ማሽኖች የመሳሰሉት እንዲሟሉ ተደርጎ የትምርቱ ሥራ ሳይጓተት በተፈለገዉ ፍጥነት እየሄደ ይገኛል፡፡
- ለወላጅ አጥ ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ ማሟያ ድጋፍ የተደረገ 165,000 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- በጎርፍ አደጋ ጉዳት የደረሰበት ኡባ ደብረ ፀሀይ ወረዳ ዛባ ቅድመ መደበኛ ት/ቤት ከ800,000 ብር በላይ የሆነ ገንዘብ ወጪ ተደርጎ ት/ቤት ግንባታ ተካህዷል፡፡
- ለሁሉም የወረዳ መዋቅሮች የማጣቀሻ መጽሐፍት እጥረት ላለበት ድጋፍ እንዲያደርጉ በ225,000 ብር የማጣቀሻ መጽሐፍት ተገዝቶ ተከፋፍሏል፡፡