የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር የ 15 ሚልየን ብር ድጋፍ አደረገ።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር በአባቢው ላይ እያከናወነ ያለውን ልማታዊ ተግባራትን በዘላቂነት ለማገዝ ያስችል ዘንድ የልማት ማህበሩ #የቦርድ_አባላት (ሥራ አስፈፃሚ ዎች) ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል።
የሚዲሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተወካይ አቶ ያዕቆብ ፍቄ ተቋማቸው የጎፋ ዕድገትና ልማት ማህበር በዞኑ በመንግሥት የማይሸፈኑ የልማት ሥራዎችን እየሠራ ያለ ማህበር በመሆኑ ልማት ማህበሩን ለማጠናከር የ 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደርጓል።
የጎፋ ዞን እድገትና ልማት ሥራ አስኪያጅ አቶ #ደግፌ#ኃይለማርያም ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለፁት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ በልማት ማህበሩ እና በዞኑ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል።
በተደረገው የድጋፍ ገንዘብ ልማት ማህበሪ ከዞኑ መንግስት ጋር በመናበብ የአከባቢውን ማህበረሰብ ልጠቅሙ የሚችሉ ቅድሚያ የተሰጣቸውን ተግባራትን እንደሚያከናውን የማህበሩ ሥራአስኪያጅ አቶ ደግፌ ኃ/ማርያም ገልጿል።
