ጎዕብማ የልማት ሥራ ትብብር ተፈራረመ

ጎዕልማ ፎሪአፍርካ(ForAfrika) ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር አብሮ ለመሥራት የልማት ትብብር ውል ተፈራረመ።

ይህ ግብረሰናይ ድርጅት በአካባቢ ጥበቃ፣ በውኃ፣ በምግብ ራስን መቻል፣ የአደጋ ስጋት ሥራዎች ላይ የምሠራ ሲሆን አሁን ከማህበራችን ጋር በአካባቢ ጥበቃ እና በምግብ ራስን መቻል ላይ ትኩረት አድርጎ ለመሥራት የውል ሰነድ ተፈራርሟል። ማህበራችን አቅም በፈቀደው በትምህርት ፣በጤና፣ በሰብዓዊ ፣ በባህል እና በማህበራዊ ዘርፎች በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ እንዳለ የምታወቅ ሲሆን በአካባቢ ጥበቃና በግብርና ዘርፍ ተሰማርቶ ለመንቀሳቀስ ጥረት እያደረገ ይገኛል ።

ስለዚህ ልማት የጋራ ጥረት የምጠይቅ ብቻ ሳይሆን ለጋራ ልማት ቅዲሚ ወይም የላቀ ትኩረት የምሻም ነው ። በመሆኑም ማህበራችን ከእያንዳንዳችን የልማት ሀሳብ፣ ዕውቀት ፣ ጉልበት ፣ገንዘብ እና ቀና እይታና ድጋፍ በምትፈልግበት ጊዜ ላይ ስለሚገኝ የልማት ድርሻችሁን እንዲትወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን ።

ለጋራ ልማት ቅዲሚያ እንሰጥ !!

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *