በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቋም የድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቋም የድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄዷል፡፡
በአደጋው ሕይወታቸው ላጡ ዜጎች የ40 ቀን መታሰቢያና ከአደጋው የተረፉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያግዝ የገቢ ማሰባሰቢያ እንዲሁም አደጋውን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ላደረጉት ድጋፍ የምስጋና መድረክ ነው በመዲናዋ የተካሄደው፡፡
የድጋፍ ማሰባሰቢያና የምስጋና መድረኩ በጎፋ ልማት ማህበር የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የጎፋ ዞን ተወላጆች አደጋውን ተከትሎ መላው ኢትዮጵያውያን ላሳዩት ድጋፍና ርብርብ ምስጋና አቅርበዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ክቡር #አገኘሁ_ተሻገር በአደጋው ለተጎዱ ቤተሰብ ልጆች/ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ቁሳቁስ ምክር ቤቱ እንደምሸፍን ቃል ገብቷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አገኘው ተሻገር፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር)፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና ሌሎችከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።



